the-tplf-mafia-group

“እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል” አለች ሕዋሀት?

“እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል” አለች ሕዋሀት?

ከወንድሙ መኰንን፣ ዩኬ፣ 06 July 2018

በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ ላይ የሚታየው የለውጥ ማዕበል ያልተጠበቀ ፈጥኖ ደራሽ ሱናሚ ይመስላል። መሣሪያ ያልያዘ የቄሮ፣ የፋኖ፣ የዘርማ እና የነበሮ ወጣቶች፣ መሣሪያ እስካአፍጢሙ ታጥቆ ከሚዋጋው ወያኔ ጦር ጋር ተጋፍጠው እጃቸውን ብቻ ከራሳቸው በላይ በማመስቀል ዘርረውት አረፉ።  እንዲህ ነው ሕዝባዊ ማዕበል ሲነሳ። ከሕዝብ ጋር ተጣልቶ ያንን ሕዝብ ማስተዳደር የማይቻል ሐቅ መሆኑን ለነዚህ ገልቱዎች ማን በነገራቸው? የወያኔ ጭንቅላት፣ ማሰብ የማይችል፣ አንጎላቸው ወደ ጡንቻ የተለወጠ ይመስላል። በዘር ጥላቻ ላይ የዘሩት ዘረኝነት፣ በቅሎ፣ አድጎ፣ ዘርዝሮ እነሱኑ እራሳቸውን መልሶ እየለበለባቸው ይገኛል። “ልክ እናስገባቸዋለን!” ባሉት ማግስት ልክ ሊገቡ ምንም አልቀርቸውም። ድግሞ ሌቦች ናቸው። ሲሰርቁ ከተያዙ መልሰው በያዛቸው ሰው ላይያፈጣሉ። ትግራይ እሾህና አመኬላ አበቀለች። ነቅላ እንዳትጥላቸው ልጆቿ ሆኑባት። እንዳታቅፋቸው፣ አርገበገቧት። ችግር ነው እናት መሆን!

ከትግራይ ውጪ በጥቅማ ጥቅም የተያዙ አገልጋዮች ነበሯቸው። እነዚያ አገልጋዮች እርጅተው እንደ አህያው “ሀረሩ” ሊጣሉ የሕወሐት የበላይነት እንዲቀጥል፣ በአዲስ ሥልጡን ምልምል ትውልድ ተተኩ። አዲሱ ትውልድ ለወያኔዎች እንደአባቶቻቸው እንደከብት የሚነዳ አልሆነላቸውም። በጉያቸው ያሳደጉት ተባባሪ እኮ የህዝብ ልጅ እንደሆነ ጨርሶ ዘንግተውታል ጃል! የወያኔ ትልቁ ድክመት ከነሱ በላይ ብልጥ የማይኖር መስሎ ስለማይታያቸው ነው። በነሱ ቤት ከነሱ በላይ፣ ጀግና፣ ከነሱ በላይ አዋቂ ላሳር ነው። እነሱ የሚናገሩትን ውሸት ዕውነት ብሎ የማይቀበል የአዕምሮ በሽተኛ ብቻ ይመስላቸዋል። ታዲያ ኦሔዴድም ሆነ ብአዴን ሙሉ በሙሉ የነሱ መሣሪያ አድርገው ስለሚያዩት እናቲቱን በገዱሉት ልጇ ሬሳ ላይ ተቀመጪ ብለው ሲያስገድዷት፣ (https://www.youtube.com/watch?v=qpu9L7W667s)  ዘመድ ወዳጆቻቹን ሲያርዱት፣ የሚሰማው አይመስላቸውም።  አማራና ኦሮሞ ከሆዱ ባሻገር ምንም የማይታየው አድርገው ከወሰዱ ዓመታት ዘልቀዋል። ያ ነው ትልቁ ውድቀታቸው።

ወያኔዎች በዘረኝነትና በከፋፍለህ ግዛ መርህ፣ ዓይናቸው ተሸብቧል። ሙሴ እኮ ከፈርዖን ቤት አድጎ ነው ዕብራውያንን መርቶ ነጻ ለማውጣት የበቃው። ግፍ ሲያዩ ያደጉት እነ ለማ መገርሳ፣ ዐቢይ አህመድ፣ገዱ አንዳርጋቸው፣ ደመቀ መኰንን የቄሮውን፣ የፋኖውን፣ የዘርማውንና የነብሮውን ድምጽ ከወያኔ ጉያ ሁነው ሰሙ። የሕዝብ የቁጣ ማዕበልን መሣሪያ እንደማያቆመው ሲረዱ፣ የተከለለላቸውን የዘር ኬላ ጥሰው “ድምህ ደሜ ነው!” ተባብለው እንደጥንቱ እንደጠዋቱ፣ ኦሮሞና አማራ አብረው ወጥተው ከሕዝብ ጎኑ ቆሙ። በጭንቅ ሰዓት ሁሌም አብረው እንደቆሙ ነው። የወያኔ መሣሪያ የሆነውን ሽፈራው ሽጉጤን የደቡብ ሕዝብ ወርወሮት ሲተባበራቸው የወያኔ የጌትነት ዘመን ወደማክተሙ ተቃረበ። ጌታቸው ረዳ፣ “እሳትና ጭድ የነበሩት ጠላቶች እንዴት ሲደረግ ነው ሊተባበሩ የቻሉት? የቤት ሥራችንን አልሠራንም ማለት ነው!” ብሎ እሪታውን ሲያቀልጥ ቪዲዮ ተቀርጾ ሲያላዝን አየነው፣ ሰማነው። ከፋፍለው መግዛታቸውን በግልጽ ማመኑን ተያያዙት! ያም ብቻ አይደለም። ለስኳር ማምረቻ የተሰጠውን ገንዘብ ጭጭ ምጭጭ ያደረገው ዓባይ ጸሐይም፣ “ለነፍስ ግድያ ይፈላለጉ የነበሩት አንድ ያደረጋቸው ሕወሀትንና የትግራይ ሕዝብን የማጥፋት ፍላጎ ት ብቻ ነው” ብሎ በሬዲዮ ሲናገር ሰማነው። አንድ ነገር አልተረዱትም። ከታሪክ እንዳየነው፣ ኦሮሞና አማራ፣ በተውልድ የተሳሰሩ ሲሆን፣ በሰላም ጊዜ በመሀላቸው የመናቆር ምልክት የሚታየው፣ ወንድማማቾች የሚጣሉት ዓይነት ጥል ነው። የኢትዮጵያ ሕለውና በተነካ ቁጥር፣ እንደ አንድ ሕዝብ ነው ተቃቅፈው የሚደምሙት። ኦሮሞና አማራ፣ ኢትዮጵያን ለማዳን ጎን ለጎን ሰሰውና ሲዋደቁ ይኸ መጀመሪያቸው አይደለም። ደማቸው በጦር ሜዳ ለኢትዮጵያ ነጻነት እንደጅረት ወርዶ ተደባልቋል። አድዋ ትመስክር! ማይጨው ትመስክር! ኦጋዴን ትመስክር! ባድሜ ትመስክር። አሁንም እኔ ከሌለሁ ኢትዮጵያን ልቧን አፈርሳለሁ የሚል የውስጥ ቦርቧሪ የአገሪቱን አንድነት ሊያናጋ ሲዝት ቢተባበሩ ምን ያስደንቃል? የነበረ፣ ያለ ነው። የሚኖርም እኮ ነው! ዕርማችሁን ዋጡት ወያኔዎች!

ከዚህ በፊት “እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ እንደሩዋንዳ ወደ እርስ በእርስ መጫረስ ትሄዳለች” በማለት ዓባይ ጸሐዬ ሲያሟርት “ምነው አቦይ ጸሐይ!” በሚል ርዕስ እሱ የሚያሟርትብን ኢትዮጵያ ውስጥ አይከሰትም ብዬ ጽፌ ነበር። “ይኼ ቤት ይቃጠላል! ብዬአለሁ” አለች አሉ እብዷ። ማታ ልታጋየው እኮ ነው። ዓባይ ጸሐዬ እኛ ከሌለን ኢትዮጵያ ትበታተናለች አለና! ያ ሕልሙ በአማራና ኦርሞ አንድነት ቀዝቃዛ ው በርዶ ተደፋበት። እሪ! ኡ! ኡ! አለ።

እነ ዓባይ ጸሐዬ በዚህ ተስፋ አልቆረጡም። ባለፈው ሰሞን ግሙዝ አሶሳ ዞኖች ዓባይ ጸሐዬ በርታዎችን በገንዘብ ገዝቶ ሲያዘምት ታየ ተባለ። ምን እየሠራ! በርታ የተብሉትን ድኃ ሕብረትሰብ ያላዩትን የገንዘብ መጠን ሰጥቶአቸው ሌሊት ሌሊት እየሄዱ አማራና ኦሮሞን ሲገደሉ ነበር! ዓባይ ጸሐዬ እንዳሰበው አልተሳካለትም። በረከት ስምዖን ቅማንቶችንና አገዎችን በአማራው ላይ ሊያነሳሳ ወሮታ አካባቢ ታይቷል። ውር ውር አብዙ። ሳሞራ ዮኑስ ጋምቤላ ምን እየሠራ ነው? በረከት ስምዖን ቅማንትና አገው መሀል ምን እየሠራ ነው። እርስ በርስ ሊያጨራርሰን!

ትግራይን “ሊያጠፉህ እየመጡብህ ነው ተዘጋጅ” ይሉታል። አቤት ክፋታቸው! አብዛኛው የትላንቱ የትግራይ ድኃ ዛሬም ያው ድኃ ነው።  ግማሹ ከትግራይ ወጥቶ ሌላ ክፍለ ሀገር ሂዶ ሲለምን የኖረው ዛሬም አዲስ አበባ መንገድ ላይ ልጇን አዝላ የምትለምን እናት ታጋጥማለች። ገበሬው ዛሬም አላለፈለትም። ሀምሳ ቢታለብ ያው በገሌ አለች አሉ ድመቲቱ!

የትግራይ ማፊያ ቢሊየነር ጄኔራሎችtplf-generals
የትግራይ ድኃ እናትold-woman-with-a-bunch-of-firewood-tigray-ethiopia-africa-dmk8wk
የትግራይ ድኃ ታዳጊ ወጣትtigray-girl-carrying-water

የትግራይ ድኃ ወጣት ሴት ልጅ ትምህርት ቤት ሳይሆን ስንት ኪሎሜትር በግሯ ተጉዛ ዛሬም ውሀ ትቀዳለች። የትግራይ አሮጊቶች አሁንም በረሀ ወርደው እንጭት ይለቅማሉ። ድኃው ከድጡ ወደ ማጡ ሆነበት። በነዚህ ድሆች ስም ነው ወያኔ የምትነግደው። በነዚህ ድኆች ትከሻ ነው ወይኔ የምትታዘለው። መጥኔ!

በሌላ በኩል፣ የትግራይ ነጻ አውጪ ቱባ ሌቦች፣ እራሳቸውን አበልጽገው፣ ለእርድ የሚቀለብ ሰንጋ መስለው ተለጥልጠው ይታያሉ። የወያኔ ጄኔራሎች በዲዛይን ልብስ ተጀብነው ውጥር ውጥር ሲሉ ዓለም የማትበቃቸው ይመስላሉ።

እንግዲህ እነዚህ አንጎላቸው በጮማ የደነዘ ቅሎቦች ናቸው ድኃው ትግሬውን “ና ሙትልኝ” እያሉ የሚጠሩት። የዝርፊያ ዘመናቸው እያጠረ ስለመጣ፣ ያንን ነባራዊ ሁኔታ ለመገልበጥ ሲሉ፣ ድኃዋን የትግሬ ሴት ብዙ መቶ ሺ ብር ለመስጠት ቃል እየገቡ፣ ቦምብ እያስታጠቁ ወደ መሀል የሚልኩት። እነዚህ ከታሊባን በምን ተለዪ? በነሱ ቤት ብልጥ ነን ባዮች በመሆናቸው፣ሲቸግር ሲቸግር፣ ሕወሀትና ትግራይ አንድ ናቸው እያሉ የአዞ እምባቸውን ይረጫሉ። በመበልጸጉ ላይ ግን፣ ድኃ ትግሬውን ከደጃቸው ድርሽ አያደርጉትም። አይሠራም!

ይህቺ እኛ ትግራይ ነን፣ ትግራይም እኛ ናት የምትለውን ድንቁርና ከየት የመጣች ናት? አረና እኮ የትግራይ ነው። Tigrean Alliance for Democracy (TAND) እኮ የትግራይ ነው። አሥራ አንድ ሺህ ጦር ይዞ ኤርትራ ውስት የመሸገው የትግራይ ኅዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትኅድን)ም እኮ የትግራይ ነው! ድንቁርናቸው በጀ እንጂ አይ ጣጣቸው!

እያወቁ ቢመናቀሩም፣ ደግመን ደጋግመን እንንገራቸው። ናዚዎች ጀርመኖች ነበሩ። ጀርመኖች ናዚዎች አይደሉም። ፋሺስቶች ጣሊያኖች ነበሩ። ጣሊያኖች ግን ፋሺስቶች አይደሉም። አሁንም ወያኖዎች ትግሬዎች ናቸው። ትግሬዎች ግን ወያኔ አይደሉም። በደፈናው እነዚህ የማፊያ ቡድን ጥርቅሞች ለትግራይ ምንም አይበጇትም። መሬት አስፋፋንልህ የሚሉት፣ ወልቃይትን፣ ጸለምትንና ሁማራን ከጎንደር ቀምተው ትግሬውን ከወንድሙ ከአማራው ጋር አናከሱት። መሬቱ ለትግራይ ባለሀብት ኢንቨስተሮች እንጂ፣ ለተራው ትግራይ ሕዝብ ምንም ነገር አይፈይድም። የትግራይን ድሆች አይደል እንዴ ቤታቸውን አፍርሰው መሬቱን ለባለጊዜዎቹ የሰጡት? ሰላም ካለ፣ የትግራይ ገበሬ፣ ወንድሙ አማራውና የኦሮሞው መሬት ላይ ሂዶ በሰላም አርሶ የማምረት፣ የመበልጸግ መብት ነበረው። ወልቃይት ውስጥ ተግሬዎች የበዙትም በዚሁ ምክንያት ነበር። ራያ ራያ እንጂ ትግሬ ነው? “ራያ ነነ! አንትንኩነ!” አለ ኑረአዲስ ሰኢድ! ሰቆጣ ወሎዬ እንጂ ትግሬ ነው? ለምን ከወሎ ጋር ሕዝቡን ማናከስ አስፈለገ? ወያኔ ሰላም አትወድም። ጭር ሲል ትረበሻለች!

ይኽች “እኛ እየገዛን፣ እየዘረፍን፣ እየገደልን፣ እያሰርን እና እያሳደድን ካልኖርን ኢትዮጵያ ትበታትን ብለው” የሞት ፍርድ በአገራችን ላይ የፈረዱባት፣ ተግባራዊ ለማድረግም ታጥቀው የተነሱት ክፉ የማፊያ ቡድን፣ እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል አለች ተብሎ ከሚተረትባት እንስሳ ምንም አየለዩም። እነሱ ካልገዙን ኢትዮጵያ ደም በደም እንደሩዋንዳ ትጭመለቅ ነው ሕልማቸው። የትግራይ ሕዝብም ቢሆን፣ ለኛ ከወንድሞቹ ከአማሮችና ኦሮምዎች ጋር ፍልሚያ ገጥሞ ይማገድ ነው ዓላማቸው። እነሱ ከሞቱ ሠርዶ አይብቀል?

ትላንት ዓላማቸው ግብ እንዲመታ ሀዋዜን ላይ ለደርግ የተሳሳተ መረጃ አስተላልፈው በሰላም ገቢያ የወጣውን ሰላማዊ ሕዝብ አስጨፍጭፈው እነሱ ግን ተደብቀው ቪዲዮ ቀርጸው ለፕሮፓጋንዳ ተጠቅመውበታል። ይኸ ክፉ ጊዜ ሲያልፍ የሚወራረድ  ሂሳብ አለ። ጨፍጫፊ ደርጎችም፣ አስጨፍጫፊ ወያኔዎችም በሕዋዜን እልቂት ላይ እኵል ተጠያቂዎች የሚሆኑበት ቀን ሩቅ አይሆንም። የሐዋዜን ደም ከሞት ሸለቆ ይጣራል!

ዛሬም ትግራይ ገብተው ዶልተው ሕዝቡ መሀል የመሸጉት ሕወሀቶች፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትዕግሥቱ አልቆ በያለበት የትግራይ ሕዝብ ጋር አንገት ላንገት ተናንቆ ቢጨራርስ ቅንጣት ታህል አይጸጽታቸውም። ነገሩ ሁሉ፣ “እኔ ከሞትኩ ሠርዶ አይብቀል” ብሄል ላይ የተመሠረተ ርዕዮታቸው ነዋ!

የትግራይ ሕዝብ ታሪክ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ማዕከል ነው። የወያኔ ባለሥልጣኖች “እምቢ ካላችሁ አንቀጽ 39ን ተጠቅመን እንገነጠላለን እያሉ እያስፈራሩን ነው። የትግራይ ሕዝብ ከመሠረታት ኢትዮጵያ ተገንጥሎ የት ሊደርስ ነው? መገንጠል ለኤርትራም አልበጀ! አንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይሄንን ማስፈራሪይ ሲሰማ፣ “ነገሩ ባቄላ አለቀ  ነው … ግን ሑመራን፣ ወልቃይትን፣ ጸለምትንና ከወሎ የመነተፋችሁትን መሬት መልሳችሁ ጥርግ ማለት ትችላላችሁ።” እያለ ነው። ያም አደገኛ አስተሳሰብ ነው። ምንኛ ብንጨክን ነው ወንድሞቻችንን ለቀን ጅቦች አስረክበን ቁጭ የምንለው። በቅርብ ጊዜ ውስጥ የትግራይ ሕዝብ ይነሳል። መብቱን ያስከብራል። እራሳችንን ከሕወህት ነጻ ማውጣት ብቻ ሳይሆን የትግራይ ወገናችንንም ከነዚህ የቀን ጅቦች የማትረፍ ግዴታ አለብን።

“እኔ ከሞትኩ ሣር አይብቀል” አለች ወያኔ!

Leave a Reply

Your email address will not be published.